Monday, October 21, 2013

አገልግሎት

በ ስ መ አ ብ ወ ወ ል ድ ወ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ አ ሐ ዱ አ ም ላ ክ አ ሜ ን!
 
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን አገልጋዮች እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።1ጴጥ 2፡5

“ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና።” ምሳ 1፡32

አገልግሎት ማለት ምን ማለት ነው?

ማንኛውንም ግብር አገልግሎት ብለን ልንጠራው እንችላለን፤ መንፈሳዊ ጥቅምም ጉዳትም የሌላቸው አገልግሎቶች አሉ፤ እንዲሁም የክፋትም አገልግሎት አለ፤ እኛ የምናነሳው አገልግሎት ከነዚህ የተለየውን አገልግሎት ነው::

መንፈሳዊ አገልግሎት ማለት ምን ማት ነው?

መንፈሳዊ አገልግሎት እንደ ስሙ ረቂቅ በሆነው መንፈሳዊ ኃይልና ጥበብ ተሞልቶ መንፈሳዊ የሆነ ረቂቅ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መስዋእትን ማቅረብ ነው፡፡ የሚያገለግለውም መንፈሳዊ አገልጋይ ይባላል፡፡

መንፈሳዊ አገልግሎት በሰውና በእግዚአብሔር እንዲሁም የእግዚአብሔር ከሆኑ ቅዱሳን ሰማእታት ጋር ቅዱሳት ነብያት ሐዋርያት ጋር እንዲሁም በቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳት በኩል በሃይማኖት የሚደረግ ግንኙነት እና ስርአተ አምልኮ ነው፡፡

ጥቅል ሃሳብ፡- አገልግሎት የክፋት አገልግሎትና ክፉ ተጋድሎ አለ፤ መንፈሳዊ አገልግሎት አለ መንፈሳዊ አገልግሎትን የምንከፍለው በሠማይ ያለ አገልግሎትን በምድር ያለ አገልግሎት ብለን ሲሆን በሠማይ ያሉ የድል ነሺዎች ሕብረትና መላእክት እግዚአብሔርን ያገለግሉታል በምድር ያለን ሰዎች (የአዳም ልጆች) ደግሞ ከድል ነሺዎቹ ሕብረት ጋር ለመቀላቀል ዋና ዓላማችንን አድርገን እናገለግላለን፡፡

1.1   መንፈሳዊ አገልግሎት በስንት ይከፈላል?

መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው ይሁን ተግባሩ አንድ ሲሆን እርሱም እግዚአብሔርን አገልግሎ ርስት መንግስተ ሰማያትን መውረስ ነው፤ ነገር ግን ለማብራራት እንዲመቸን አገልግሎት በምድራዊ ሕይወት ሳለን ለሦስት መክፈል እንችላለን፡-

ሀ) ራስን ማገልገል

ለ) ሕዝብን ማገልገል

ሀ) ራስን ማገልገል ፡- ማለት አስቀድሞ ራስን በመንፈሳዊ ምግባራት መገንባት ራስን ከኃጢያትና ከክፉ ተግባራት በመጠበቅ ሁል ጊዜም ቢሆን ከሁሉ አስቀድሞ እራስን መመርመር ነው፤ በጥቅሉ እራስን ማስተማር፣ መገሠጽ፣ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በስግደት መትጋት፣ ዘወትር ቅዱሳት መጽሐፍትን ማንበብ፣ ሊቃውንትንና ተርታውን ሰውም ቢሆን መጠየቅና ከእነርሱ መማር የመሳሰሉትን መፈጸም ማለት ነው፡፡

አገልግሎት የሚታይ ምግባር ስለሆነ አንድ አገልጋይ የምግባር ሕይወትን በመያዝና በቃል የተማረውን ትምህርት በተግባር ሲተረጉመው ራሱን አገለገለ ይባላል፤ ሎጥ ራስህን አድን እንደተባለ ሰውን ከማንሳቱ በፊት ራሱ መነሳት፤ ሰውን ከማዳኑ በፊት ራሱን ማዳንን የሚተገብር ነው፡፡

ራስን ማገልገል ያለው ጠቀሜታ፡ በቅድሚያ ከራስ መጀመር እንደ መርፌ ታላላቅ ቀዳዳዎችን ሁሉ እየሰፉ የራስን ትንሽ ቀዳዳ መመልከት አለመቻልን ያርቃል፤ እንደ መቋሚያ ሰዎችን ሁሉ እያዎመ ራሱ ግን ብቻውን መቆም የማይችል እንዳይሆን ሰዎችን አብርቶ ለራቱ ጨለማ ሰዎችን አገልግሎ እርሱ የተጣለ እንዳይሆን ይጠቅመዋል፤ ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ።” 1ቆሮ ፡19 እንዲሁም “ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።” ብሎ ሐዋርያው 1ቆሮ 9፡27 እንደተናገረ፡፡

·         ስለዚህም በቅድሚያ ራስን ማገልገል ለሕዝባዊ አገልግሎት ዋና መሰረት ይሆነናል፡፡

·         ራስን ማገልገል ጉዳት አለው ን? ራስን ማገልገል ጉዳት ኖሮበት ሳይሆን ራስን ብቻ አገልግሎ ለራስ ብቻ ኖሮ ማለፍ ራስን እንጂ እግዚአብሔርን አገለገልን ስለማይባል ተገቢ አይሆንም፤ የሕዝብንና የእግዚአብሔርን አገልግሎት ትተን በራሳችን ዙሪያ ብቻ የምናተኩር ከሆነ በእግዚአብሔር ቤትና ፍቅራችን ላይ ላለው ግንኙነት ጥያቄ ምልክት ይፈጥርብናል ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ ፍጻሜው እኛን ያለዋጋ ያስቀረናል ማለት ነው፡፡

·         ይህን መሰል ችግር እንዳይፈጠር ምን ማድረግ አለብን? ይህ ችግር እንዳይከሰት ማድረግ ካሉብን ዋና ዋና ነገሮች መካከል

1)     በጋራ ጸሎት መታጋት፡፡

2)    የራስን ደካማነት መገንዘብና በሕብረት መንፈሳዊ ኑሮ ማመን፡፡

3)    ከራስ ወዳድነት ስሜት መላቀቅ

4)     . . .

በምድር ያለ መንፈሳዊ አገልግሎት  እግዚአብሔርን ማገልገል ራስን እና ሕዝብን ማገልገል ብለን ልንከፍለው እንችላለን ወይም ሕዝብን በማገልገል ራስም ማገልገል ብለን ልንገልጸው እንችላለን፤ እዚህ ላይ ሕዝብ ስንል ማንኛውንም የሰው ልጅ በቅንነትና በፈርሃ እግዚአብሔር ተሞልተን ካገለገልን እግዚአብሔር እንደዋጋ ይቆጥርልናል ምዕመናንን ብቻ ወይም የቤተክርስቲያን አባቶችን ብቻ የተገደበ አይደለም፤ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ወደ መዳን እንዲደርሱ ዓላማው ነውና ይህን አላማ እናገለግላለን፤ መንፈሳዊ አገልግሎት በጥልቅ ትርጓሜው የእግዚአብሔርን ዓላማ ማገልገል ማለት ነው፡፡

ለ) ሕዝብን ማገልገል

ሕዝብን ማገልገል ማለት በማሕሌት በቅዳሴና በመዝሙሩ የእግዚአብሔር የሆኑትን ምእመናንን ማገልገል ማለት ሲሆን፤ በማሕበራዊ ሕይወቱ ውስጥ ደግሞ አንድ መንፈሳዊ አገልጋይ ሕብረተሰቡን ሁሉ ዘር፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለይ ለሁሉም በቅንነት ይታዘዛል ያገለግላል፤ይህም በጻድቁ ዮሴፍና በፋርስ ምርኮ በነበሩት በዳንኤልና በሦስቱ ህጻናት ተገልጻል፡፡

ሕዝብን ማገልገል በግል ይልቅ መንፈሳዊ ሕይወትን በጋራ መምራት ማለት ነው፤ በሕዝባዊ አገልግሎት ውስጥ የምናገኘው ጥቅም በሕዝባዊ አገልግሎታችን ውስጥ እግዚአብሔርንና ራሳችንን በአንድነት ስለምናገለግልበት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እጅግ የተወሳሰበ አቅጣጫ ውስጥ ገብቶ የነበረንና ከጭንቀቱ የተነሳ ራሱን የማጥፋት ውሳኔ ላይ የደረውን ሰው እግዚአብሔር እንደየአቅማችን በሰጠን ሕያው ቃሉ አጽናንተን መክረንና ገስጸን ብንመልሰው፤ ሦስት ጥቅሞች ይገኛሉ፡ -

1) የልጁ ደማዊ ነፍስ ብቻ ሳትሆን ሕያዊት ነፍሱንም እናድንበታለን፡፡

2) እግዚአብሔር ማንም እንዲጠፋ ፈቃዱ ስላልሆነ የአንድ ሰው መዳን በእግዚአብሔርና በመላእክቱ እንዲሁም በሠማይ ያሉ ቅዱሳን ሁሉ ይደሰታሉ፡፡

3) በፍጻሜው ግን ራሳችን ዋጋን እናገኝበታለን ስለዚህም ሦስቱም ጥቅሞች በሕዝባዊ አገልግሎት በምንለው ውስጥ ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ የምንመለከተውና ግልጽ ሊሆንልን የሚገባው ነገር ሕዝባዊ አገልግሎት ስንል ቁጥራቸው እጅግ የበዛውን ሰዎች ብቻ ማለት አይደለም ሕዝባዊ አገልግሎት በምናገለግላቸው ሰዎች ቁጥር አይወሰንም ጌታችን አንዲት ሳምራዊ ሴትና እንዲሁም ፈሪሳዊውን ሊቅ ኒቆዲሞስን በማታ ለብቻቸው አስተምሮ አድኗልና፡፡ የእርሱን አርአያ ተከትለን የምንጓዝ የዛሬዎቹ አገልጋዮች ደግሞ እርሱን አብነት አድርገን በሰው ብዛት ሳይሆን አንድም ሰው ቢሆን ለማገልገል ዝግጁ መሆን ለአንዲት ነፍስ ልንራራ ልንቆረቆር ይገባል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሕዝባዊ አገልግሎት በምናገለግላቸው ሰዎች ማንነት፣ የምናገለግልበት ቦታ፣ ወዘተ አይወሰንም

ብራብ አብልታችሁኛል የሚለው ቃል በስጋ ተርበው የምናበላቸውን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን የቃሉን ወተት የተራቡትን ስጋ ወደሙን በማጣት ድርቅ የተያዙትን መመገብ ፤ ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆቱትን ማልበስ፤ በኃጢያት ወኅኒ እስራት የተያዙትን ማስፈታት፣ ጾር ከብዶባቸው የታመሙትን መጠየቅ ማበርታት ነው፡፡

የሕዝባዊ አገልግሎት ጉዳት ይኖረው ይሆን?

ከአገልግሎቱ ሳይሆን ከስጋዊ ድካም ልንታበይ እንችላለን እንዲሁም የእነርሱን ፈቃድ መፈጸም እግዚአብሔርን ማገልገል መስሎን ባለማስተዋል ከእግዚአብሔር ትዕዛዝና ሃሳብ ፈቀቅ ልንል እንችላለን፡፡ ይህን መሰለ ችግር እንዳይከሰትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ዘወትር በጸሎት መጠየቅና የእርሱን ፈቃድና ሃሳብ ምን እንደሆነ መማር ያስፈልጋል፡፡

ሌላው ከራስ መንፈሳዊ ድካም የሚመጣና ባለማስተዋል ታይታንና ሌሎች አላስፈላጊ የሆኑ ስጋዊ ነገሮችን ልናስብ እንችላለን፤ ይህም አንዱ ተግዳሮት ነው፡፡ ሰውንና እግዚአብሔርን አገልግሎ ያለዋጋ መቅረትም አለ፡፡


 

እግዚአብሔርን ማገልገል ስንል ምን ማለታችን ነው?

እግዚአብሔርስ በምን በምን ይገለገላል? በገንዘብ በጉልበት በዕውቀት

ሰላም፣ መንፈሳዊ እርካታ፣ መንፈሳዊ ደስታ፣ በአገልግሎ ይገኛል፤ ቅዱስ መንፈስ ሲቀርበት ጠላት ይርቀናል ሕይወታችንም ይባረካል፡፡

ጊዜና ጉልበታችንን አባክነን በረከት ማግኘት ሲገባን በከንቱ ምኞትና ሃሳብ ዋጋችንን ማጣት የለብንም፡፡

የሴቶች አገልግሎት፡- የጳውሎስን መልእክት በማመላለስ፣ ትንሳኤውን በማብሰር 36ቱ ቅዱሳን አንስት በወንጌል አገልግሎት ላይ በመተባበር . . .

የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ዘዳ 4፡9-10 መርሃ ግብር መምራት ማስተባበር መዘመር ቅዳሴና ጸሎቶች ማህሌቱ ላይ በመሳተፍ

የአገልግሎት ሕይወት ሉቃ 12፡42 1ጢሞ 3፡5

·         በአገልግሎት መሰልቸት ምንድን ነው? መንፈሳዊ ዝለትስ? የሚሰለቹ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?

በሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኘው የወጣቱ ሕብረት ትልቅ ኃይል ስለሆነ ለቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤትን ትልቅ ስራን መስራት የሚችል ጥሩ አደረጃጀት ያለው ብርቱ ተቋም አድርጎታል፡፡

ከኦሪት ጊዜ ጀምሮ ልጆችና ወጣቶች በጉብዝና ወራት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማሩና በጋራ እንዲሰባሰቡ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳስባል ዘዳ 4፡9-10

የክህነት አገልግሎት

-       በአሁኑ ጊዜ ክህነት ለሁሉ ሕዝብ ዘርን ሳይመርጥ ተባእት ጾታ ለሆነ ሁሉ የሚሰጥ ሲሆን፤ በፊት ዘር ከፈቀደ ብቻ ካህን መሆን ሲቻል አሁን ግን እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲሆን ብቻ በክህነት እርሱን ማገልገል እንችላለን፡፡

-       ለመምከር፣ ለመገሰጽ፣ ለመስበክ፣ ለማጽናናት፣ ለማጥመቅ፣ ስጋ ወደሙን ለማቀበል፣ ቤተክርስቲያንን በማስተዳደር የጸሎት ስርዓቶችን ለመምራት፣ በቅዳሴ በማኅሌቱ ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ሆነው የሚያገለግሉ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ተሳትፎ ያላቸው ታላቅ አገልጋዮች ናቸው ካህናት (ከድቁና እስከ ጵጵስና)፡፡

-       አንድ ካህን በአገልግሎቱ ሉቃ 12፡42፣ 1ጢሞ 3፡2-8፣ ሮሜ 15፡16፣ ቲቶ 1፡7 እኚህንና የመሳሰሉትን ነጥቦች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡ ከምንም ነገር በላይ ለመንጋው የሚራራ መሆን ይኖርበታል፡፡

-       የምናገለግለው ለምንድን ነው? ዘለዓለማዊ መንግሥት ምንድን ነው?

-       በአገልግሎት መሰላቸትና መንፈሳዊ ዝለት ከምን ይመጣል? አገልግሎት የሚሰለቻቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው የማይሰለቻቸውስ?

o   ጥያቄዎች

-       አገልግሎት ምንድን ነው?

-       አገልግት እንዴት እናገለግላለን?

-       ምን ዓይነት አገልግሎት

-       አገልግሎት ለምን እናገለግላለን? ባናገለግልስ ምን እንጎዳለን? የማገልገል ጥቅሙስ ምንድን ነው?

-       በአገልግሎት መሰላቸት ምክንያቱ ምንድን ነው? ለምን እንሰለቻለን? እንዳንሰለች ምን ማድረግ አለብን? ምን ዓይነት አገልግሎት ነው የማይሰለቸን? የሚሰለቹና የማይሰለቹ ሰዎች ልዩነታቸው ምኑ ላይ ነው?

-       የምናገለግለው በምን ሰዓት ነው? በሙሉ ሰዓት ማገልገል ምን ማለት ነው?

-       የቅዱሳን አባቶቻችን አገልግሎት ከእኛ አገልግሎት የሚለዩባቸው ነጥቦች ምን ምን ናቸው? እኛስ እንደ እነርሱ ለማገልገል ምን ማድረግ አለብን?

-       አገልግሎት የምንሰጥበት ቦታ የት ነው? ለምን ዓይነት ሰዎች ነው?

-       በአገልግሎት የምናገኘው ዓብይ ጥቅም ምንድን ነው? ጉዳትስ አለው ወይ?

-       አገልግሎት ውስጥ ለመግባት ምን ያስፈልጋል? ከአገልግሎት በፊት፣ ውስጥና ድሕረ አገልግሎት አገልጋይ ምን መምሰል አለበት?

-       ወደ አገልግሎት እንዳንሄድ የሚገዳደሩን ነገሮች ምን ምን ናቸው?

-       የአገልግሎት ምርጫ፣ ጸጋና የክፍል ምደባ ምንድን ነው? እንዴት እንወስናለን እንመርጣለን?

-       ለወደፊት ምን ማድረግ አለብን?

-       አገልጋይ ለቤተሰብና ለሕብረተሰቡ ትልቅ አርአያ ነው፡፡

 

“እኔ ለእነርሱ መምህር ነኝ በአንተ ክፍል ውስጥ ግን ተማሪ ነኝ፤ እኔ የእነርሱ እረኛ ብሆንም ከአንተ መንጋ በጎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡” ቅዱስ አውግስጢኖስ

No comments:

Post a Comment