Monday, October 21, 2013

“ላሚቷ ነጭ ፤ ወተቷ ጥቁር”


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!





የጽሑፉ ዓላማው፡- ውጫዊ የሆነ መንፈሳዊነት ብቻ ደምቀን ውስጣችን ግን በመረረ ፍሬና ክፉ ምግባር የሆነብን ሰዎችን መምከር

ዶሮ አራት መአዘን እንቁላል ጥላ አታውቅም በግ ፍየልን ወልዳ አታውቅም ሁሉን ስነ ፍጥረት እግዚአብሔር አምላካችን በሚመራቸው ሕግ ታዘው ይመራሉ፤ የዛሬ 1000 ዓመት በፊቱ በሬ አሁንም በሬ ነው፤ አሁን ተነስቼ የምነቸውን ሳር ትቼ ስጋ በል ልሁን አላለም፤ የሰው ልጅ ግን እንዳስቀመጡጥ የማይገኝ ዕቃ የተባለውን የማይሰማ አማጺ ነው፤ የተከሉበት በመገኘት ዛፍ እንኳን ይበልጠናል ተነቅሎ ሌላ ቦታ አይሄድምና የእኛ የሰዎች ክፋት እግዚአብሔር እንኳን በሰው ልጅ ግብር እጅግ አዝኗል ቃላት ስላልተገኘለትም ለባሕሪው የማይስማማውን ጸጸት እንኳን ተጸጸተ እስኪባል ድረስ ከተፈጥሮ ውጪ ሲከውን የሰው ልጅ ተገኝቷል፡፡

በአንድ ወቅት አንዲት ላም ነበረች አሉ፤ ይህቺ ላም በለምለሙ መስክ ላይ ተሰማርታ እንደ ፈለገች እየቧረቀች ያሻትን ሳርና ቅጠል እየቀነጠበች ትውል ነበር በጣም ደስተኛ ትመስላለች ስትታይ፤ ደግሞ ሌሎቹ ላሞችም ለእርሷ ልአክብሮት ይሰጧታል፤ ነጭ ነቻ! የምታምር ነጭ ላም፣ በውበቷ እንደ እርሷ የተጠቀም የላም ዘር የለም መቼም፤ ስትሔድ ለሳሩ እንኳን አታዝንለትም ዳግም አንገቷን ደፍታ የምትግጠው እንኳን እስክትመስል ድረስ አንገቷን እንደ ዝንብ ማባረሪያ ጭራ እወዲያና እወዲህ እያደረገች ምንም ስራ ባይኖራት እንኳን ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ትሄዳለች፣ ተንጎራደዳለች፡፡

አይደርሱ የለ ያ ቀን ደረሰ፡፡ የቱ? አትሉኝም መታለቢያዋ ነዋ፤ ለአቅመ ላምነት ደርሳለችና መሳያን ጥጃ አፍርታ እንገሩን ከአጠባች በኃላ ባለቤቶቹዋም ከበለሳቸው ለምግብነት ፍሬን እንደሚጠብቁ ከእርሷም የሚጠጡትን ወተት ፈለጉ፤ የምታልበው ገረድ ከስር መደቀኛዋን ይዛ ጥጃዋን ከላሟ ፊት ለፊት አስራ ስታበቃ የላሟን የወተት ምንጭ በእጆቹዋ ይዛ በጥበብ ወተቱን ጠራችው፤ አንድ ሁለት ሦስት ጊዜ ሷ . . ሷ . . ሷ . . ካደረገች በኋላ ወደ እቃዋ ብትመለከት ያልጠበቀችውን የወተት አይነት ተመለከተች በአግራሞት ጎነበስ ካለችበት ቀናብላ ደግማ ከወተቷ ጨመረችበት “ከዕቃው ነው? ወይስ. . ; አለች በአግርሞት በመጨረሻ ግን አረጋገጠች ጥጃው ለካ እንደዚህ ወተቷን የተጸየፈውና የከሳው እንገር ነው ብሎ የጠባው ችግር ስለሆነ ነው! ከላይ የሚገርም ካባ አልብሶነበር ታዲያ የት አለ ዋናው ቁም ነገሩ፤ አለቻት ላሚቷ ትሰማት ይመስል እያዋራቻት፤ መልስ ስላጣች በዝምታዋ ተናዳ ገረዷ ቀጠለች እኛ አንቺን የቁንጅና ውድድር ለማሳተፍ እኮ አይደለም ቀን ከሌት እየለፋን የምንቀልብሽ አለቻት በንዴት፤ በዚህን ሰዓት ላሟ መልስ ብቻ አይደለም የሚመልስላት እንኳን አጣች መቼስ ፋንድያ የሚዝቀው እንዳይከራከርላት እርሱ ለራሱ አላፈራ ብሎ ያስቸገረ የበለስ ዛፍ ስራ ጠምዶታል፤ አላቢ ገረዷ በይ ለአሁን እሺ ለነገ ግን ይኼን ወተት ቀይረሽ እንዳገኝሽ አለቻት ለላሟ በማሰብ በተማጽኖ፤ ላሟ ጥሩ እድል ነበር የገኘችው ነገር ግን ላሟ ይባስ ብላ፤ ይኼ ምንሆነና ነው የምቀይረው ከዚህ ቀደም የነበሩት ላሞች ማምጣት ያልቻሉትን ልዩና በጣዕሙ አዲስ ወተት ስላቀረብኩ ነው፤ ብላ አንድ ቅንድቧን ወደ ተራራ አንዱን ደግሞ ወደ ጎተራው አመሳቅላ በቁጣ ተናገረቻት ይባስ ብላ የቀድሞውን ስርዓት ናፋቂ ለውጥ ጠላት አይሁድ ባላ ሰደበቻት ላሟ ከየት እንደ ሰማችው እግዚር ይወቀው ግን አለቻት፤ አሁን አሁን ዲሽም እበረት ውስጥ ሳይኖር አይቀርም መሰለኝ፡፡

ምናለበት ላሟ የነገሯትን ብትሰማ ልጇን ያልሆነ ወተት አጥብታ ከምትጎዳው እኛም ከእርሷ ሳንጠቀም አብልተን አብልተን ከምንከስር ትክክለኛ ወተት ብትሰጥ . .  አልኩኝ ለራሴ፤ እውነት ላሟ ትቁር ሆና ወተቷ ነጭ ቢሆን ብዙዎች በተጠቀሙ አልኩኝ አንዳንድ ከሌላ ከበረቱ ውጪ የተወለዱ ጥጃዎች የላሟን ልዩ ወተት አዲስ ነገር በሚል ፈሊጥ አብረዋት ሲከራከሩ ሰምቻለሁ፡፡

አሁን አሁን የክርስቲያን ወገኖች ከወተቱ ይልቅ ወደ ሌጦው እያዘነበልን የመጣንበት ከላይ ያማረ መሳይ ፍሬና ወተት ግን ሲፈለግበት ተራ ሰዎች የበዛንበት ዘመን ላይ እገኛለን፤ ለምን ይሆን? ብዙ አስተማሪዎች ብቅ ብለዋል እናት ቤተ ክርስቲያናችንም ማኅጸንዋ ከመውለድ አልነጠፈምና በየዘርፉ አገልጋዮች ፈርተዋል ሊመግቡን ሲመጡ ግን እንደ እሬት የመረረና ጣእም አልባ ወተት ያላቸው ተበራክተዋል፤ ግርማ ሞገስና አለባበሳቸው ብቻ አምሮ ፍሬያቸውን እንደ ቀደምት አባቶቻችን ካላሳዩን ምንድን ነው ትርጉሙ; አበው አስቀድመው ዳዋ ለብሰው ጤዛ ልሰው ዋሻ ምሰው በዱር በገደሉ እየተዘዋወሩ በሰው ዓይን ውስጥ የሚገባ ሰውነትና ልብስ እንኳን አልነበራቸውም ነገር ግን በጸጋ እግዚአብሔር የተቃኘ ትምህርታቸው ዛሬም ድረስ ህያው ሆኖ ከነፍስ ደዌ ይፈውሰናል፡፡

እግዚአብሔር ሁሌም ልቡናችንን ነው የሚያየው “ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” ተብሎ ተጽፏልና 1ሳሙ 16፡7 እንዲሁም ከእኛ የሚፈልገው እንቅስቃሴያችንን፣ ግርማ ሞገሳችንን፣ በሳሙና አጥበን የለበስነውን ልብሳችንን አይደለም “ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ” አለ እንጂ ምሳ 23፡26፤ ቅጠላችን አምሮ መራራ ፍሬን አናፍራ ከላሟ ቆዳ ወተቷ ልጆችን እንደሚያሳድግ እንወቅ በሃይማኖት ያልጎለመሱ የቃሉን ወተት የሚመኙ አሉና ስለወተቱ እንጠንቀቅ፤ ላሟም ምንም እንስሳ ብትሆንም የሚያስከብራትና ጌታዋ ቤት የሚያኖራት ወተቷና ሊያርስና ሊያገለግል የሚችል የፈረጠመ ኮርማ በሬ ማፍራት ስትችል ነው፤ እኛም በጌታችን ቤት እየኖርን ቃሉን ተቀልበን ስንኖር ሁሌም ፍሬ ይጠበቅብናል የክርስትና ውጤቱ እግዚአብሔር እንዲከብርብን አፍርተን መገኘት ነው፤ በውጭ መድመቅና መብረቅረቅ ገበያ ላይ ለሚያታልሉን ዕቃዎች እንኳን አልበጀምና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አገልግሎት

በ ስ መ አ ብ ወ ወ ል ድ ወ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ አ ሐ ዱ አ ም ላ ክ አ ሜ ን!
 
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን አገልጋዮች እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።1ጴጥ 2፡5

“ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና።” ምሳ 1፡32

አገልግሎት ማለት ምን ማለት ነው?

ማንኛውንም ግብር አገልግሎት ብለን ልንጠራው እንችላለን፤ መንፈሳዊ ጥቅምም ጉዳትም የሌላቸው አገልግሎቶች አሉ፤ እንዲሁም የክፋትም አገልግሎት አለ፤ እኛ የምናነሳው አገልግሎት ከነዚህ የተለየውን አገልግሎት ነው::

መንፈሳዊ አገልግሎት ማለት ምን ማት ነው?

መንፈሳዊ አገልግሎት እንደ ስሙ ረቂቅ በሆነው መንፈሳዊ ኃይልና ጥበብ ተሞልቶ መንፈሳዊ የሆነ ረቂቅ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መስዋእትን ማቅረብ ነው፡፡ የሚያገለግለውም መንፈሳዊ አገልጋይ ይባላል፡፡

መንፈሳዊ አገልግሎት በሰውና በእግዚአብሔር እንዲሁም የእግዚአብሔር ከሆኑ ቅዱሳን ሰማእታት ጋር ቅዱሳት ነብያት ሐዋርያት ጋር እንዲሁም በቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳት በኩል በሃይማኖት የሚደረግ ግንኙነት እና ስርአተ አምልኮ ነው፡፡

ጥቅል ሃሳብ፡- አገልግሎት የክፋት አገልግሎትና ክፉ ተጋድሎ አለ፤ መንፈሳዊ አገልግሎት አለ መንፈሳዊ አገልግሎትን የምንከፍለው በሠማይ ያለ አገልግሎትን በምድር ያለ አገልግሎት ብለን ሲሆን በሠማይ ያሉ የድል ነሺዎች ሕብረትና መላእክት እግዚአብሔርን ያገለግሉታል በምድር ያለን ሰዎች (የአዳም ልጆች) ደግሞ ከድል ነሺዎቹ ሕብረት ጋር ለመቀላቀል ዋና ዓላማችንን አድርገን እናገለግላለን፡፡

1.1   መንፈሳዊ አገልግሎት በስንት ይከፈላል?

መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው ይሁን ተግባሩ አንድ ሲሆን እርሱም እግዚአብሔርን አገልግሎ ርስት መንግስተ ሰማያትን መውረስ ነው፤ ነገር ግን ለማብራራት እንዲመቸን አገልግሎት በምድራዊ ሕይወት ሳለን ለሦስት መክፈል እንችላለን፡-

ሀ) ራስን ማገልገል

ለ) ሕዝብን ማገልገል

ሀ) ራስን ማገልገል ፡- ማለት አስቀድሞ ራስን በመንፈሳዊ ምግባራት መገንባት ራስን ከኃጢያትና ከክፉ ተግባራት በመጠበቅ ሁል ጊዜም ቢሆን ከሁሉ አስቀድሞ እራስን መመርመር ነው፤ በጥቅሉ እራስን ማስተማር፣ መገሠጽ፣ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በስግደት መትጋት፣ ዘወትር ቅዱሳት መጽሐፍትን ማንበብ፣ ሊቃውንትንና ተርታውን ሰውም ቢሆን መጠየቅና ከእነርሱ መማር የመሳሰሉትን መፈጸም ማለት ነው፡፡

አገልግሎት የሚታይ ምግባር ስለሆነ አንድ አገልጋይ የምግባር ሕይወትን በመያዝና በቃል የተማረውን ትምህርት በተግባር ሲተረጉመው ራሱን አገለገለ ይባላል፤ ሎጥ ራስህን አድን እንደተባለ ሰውን ከማንሳቱ በፊት ራሱ መነሳት፤ ሰውን ከማዳኑ በፊት ራሱን ማዳንን የሚተገብር ነው፡፡

ራስን ማገልገል ያለው ጠቀሜታ፡ በቅድሚያ ከራስ መጀመር እንደ መርፌ ታላላቅ ቀዳዳዎችን ሁሉ እየሰፉ የራስን ትንሽ ቀዳዳ መመልከት አለመቻልን ያርቃል፤ እንደ መቋሚያ ሰዎችን ሁሉ እያዎመ ራሱ ግን ብቻውን መቆም የማይችል እንዳይሆን ሰዎችን አብርቶ ለራቱ ጨለማ ሰዎችን አገልግሎ እርሱ የተጣለ እንዳይሆን ይጠቅመዋል፤ ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ።” 1ቆሮ ፡19 እንዲሁም “ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።” ብሎ ሐዋርያው 1ቆሮ 9፡27 እንደተናገረ፡፡

·         ስለዚህም በቅድሚያ ራስን ማገልገል ለሕዝባዊ አገልግሎት ዋና መሰረት ይሆነናል፡፡

·         ራስን ማገልገል ጉዳት አለው ን? ራስን ማገልገል ጉዳት ኖሮበት ሳይሆን ራስን ብቻ አገልግሎ ለራስ ብቻ ኖሮ ማለፍ ራስን እንጂ እግዚአብሔርን አገለገልን ስለማይባል ተገቢ አይሆንም፤ የሕዝብንና የእግዚአብሔርን አገልግሎት ትተን በራሳችን ዙሪያ ብቻ የምናተኩር ከሆነ በእግዚአብሔር ቤትና ፍቅራችን ላይ ላለው ግንኙነት ጥያቄ ምልክት ይፈጥርብናል ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ ፍጻሜው እኛን ያለዋጋ ያስቀረናል ማለት ነው፡፡

·         ይህን መሰል ችግር እንዳይፈጠር ምን ማድረግ አለብን? ይህ ችግር እንዳይከሰት ማድረግ ካሉብን ዋና ዋና ነገሮች መካከል

1)     በጋራ ጸሎት መታጋት፡፡

2)    የራስን ደካማነት መገንዘብና በሕብረት መንፈሳዊ ኑሮ ማመን፡፡

3)    ከራስ ወዳድነት ስሜት መላቀቅ

4)     . . .

በምድር ያለ መንፈሳዊ አገልግሎት  እግዚአብሔርን ማገልገል ራስን እና ሕዝብን ማገልገል ብለን ልንከፍለው እንችላለን ወይም ሕዝብን በማገልገል ራስም ማገልገል ብለን ልንገልጸው እንችላለን፤ እዚህ ላይ ሕዝብ ስንል ማንኛውንም የሰው ልጅ በቅንነትና በፈርሃ እግዚአብሔር ተሞልተን ካገለገልን እግዚአብሔር እንደዋጋ ይቆጥርልናል ምዕመናንን ብቻ ወይም የቤተክርስቲያን አባቶችን ብቻ የተገደበ አይደለም፤ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ወደ መዳን እንዲደርሱ ዓላማው ነውና ይህን አላማ እናገለግላለን፤ መንፈሳዊ አገልግሎት በጥልቅ ትርጓሜው የእግዚአብሔርን ዓላማ ማገልገል ማለት ነው፡፡

ለ) ሕዝብን ማገልገል

ሕዝብን ማገልገል ማለት በማሕሌት በቅዳሴና በመዝሙሩ የእግዚአብሔር የሆኑትን ምእመናንን ማገልገል ማለት ሲሆን፤ በማሕበራዊ ሕይወቱ ውስጥ ደግሞ አንድ መንፈሳዊ አገልጋይ ሕብረተሰቡን ሁሉ ዘር፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለይ ለሁሉም በቅንነት ይታዘዛል ያገለግላል፤ይህም በጻድቁ ዮሴፍና በፋርስ ምርኮ በነበሩት በዳንኤልና በሦስቱ ህጻናት ተገልጻል፡፡

ሕዝብን ማገልገል በግል ይልቅ መንፈሳዊ ሕይወትን በጋራ መምራት ማለት ነው፤ በሕዝባዊ አገልግሎት ውስጥ የምናገኘው ጥቅም በሕዝባዊ አገልግሎታችን ውስጥ እግዚአብሔርንና ራሳችንን በአንድነት ስለምናገለግልበት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እጅግ የተወሳሰበ አቅጣጫ ውስጥ ገብቶ የነበረንና ከጭንቀቱ የተነሳ ራሱን የማጥፋት ውሳኔ ላይ የደረውን ሰው እግዚአብሔር እንደየአቅማችን በሰጠን ሕያው ቃሉ አጽናንተን መክረንና ገስጸን ብንመልሰው፤ ሦስት ጥቅሞች ይገኛሉ፡ -

1) የልጁ ደማዊ ነፍስ ብቻ ሳትሆን ሕያዊት ነፍሱንም እናድንበታለን፡፡

2) እግዚአብሔር ማንም እንዲጠፋ ፈቃዱ ስላልሆነ የአንድ ሰው መዳን በእግዚአብሔርና በመላእክቱ እንዲሁም በሠማይ ያሉ ቅዱሳን ሁሉ ይደሰታሉ፡፡

3) በፍጻሜው ግን ራሳችን ዋጋን እናገኝበታለን ስለዚህም ሦስቱም ጥቅሞች በሕዝባዊ አገልግሎት በምንለው ውስጥ ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ የምንመለከተውና ግልጽ ሊሆንልን የሚገባው ነገር ሕዝባዊ አገልግሎት ስንል ቁጥራቸው እጅግ የበዛውን ሰዎች ብቻ ማለት አይደለም ሕዝባዊ አገልግሎት በምናገለግላቸው ሰዎች ቁጥር አይወሰንም ጌታችን አንዲት ሳምራዊ ሴትና እንዲሁም ፈሪሳዊውን ሊቅ ኒቆዲሞስን በማታ ለብቻቸው አስተምሮ አድኗልና፡፡ የእርሱን አርአያ ተከትለን የምንጓዝ የዛሬዎቹ አገልጋዮች ደግሞ እርሱን አብነት አድርገን በሰው ብዛት ሳይሆን አንድም ሰው ቢሆን ለማገልገል ዝግጁ መሆን ለአንዲት ነፍስ ልንራራ ልንቆረቆር ይገባል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሕዝባዊ አገልግሎት በምናገለግላቸው ሰዎች ማንነት፣ የምናገለግልበት ቦታ፣ ወዘተ አይወሰንም

ብራብ አብልታችሁኛል የሚለው ቃል በስጋ ተርበው የምናበላቸውን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን የቃሉን ወተት የተራቡትን ስጋ ወደሙን በማጣት ድርቅ የተያዙትን መመገብ ፤ ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆቱትን ማልበስ፤ በኃጢያት ወኅኒ እስራት የተያዙትን ማስፈታት፣ ጾር ከብዶባቸው የታመሙትን መጠየቅ ማበርታት ነው፡፡

የሕዝባዊ አገልግሎት ጉዳት ይኖረው ይሆን?

ከአገልግሎቱ ሳይሆን ከስጋዊ ድካም ልንታበይ እንችላለን እንዲሁም የእነርሱን ፈቃድ መፈጸም እግዚአብሔርን ማገልገል መስሎን ባለማስተዋል ከእግዚአብሔር ትዕዛዝና ሃሳብ ፈቀቅ ልንል እንችላለን፡፡ ይህን መሰለ ችግር እንዳይከሰትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ዘወትር በጸሎት መጠየቅና የእርሱን ፈቃድና ሃሳብ ምን እንደሆነ መማር ያስፈልጋል፡፡

ሌላው ከራስ መንፈሳዊ ድካም የሚመጣና ባለማስተዋል ታይታንና ሌሎች አላስፈላጊ የሆኑ ስጋዊ ነገሮችን ልናስብ እንችላለን፤ ይህም አንዱ ተግዳሮት ነው፡፡ ሰውንና እግዚአብሔርን አገልግሎ ያለዋጋ መቅረትም አለ፡፡


 

እግዚአብሔርን ማገልገል ስንል ምን ማለታችን ነው?

እግዚአብሔርስ በምን በምን ይገለገላል? በገንዘብ በጉልበት በዕውቀት

ሰላም፣ መንፈሳዊ እርካታ፣ መንፈሳዊ ደስታ፣ በአገልግሎ ይገኛል፤ ቅዱስ መንፈስ ሲቀርበት ጠላት ይርቀናል ሕይወታችንም ይባረካል፡፡

ጊዜና ጉልበታችንን አባክነን በረከት ማግኘት ሲገባን በከንቱ ምኞትና ሃሳብ ዋጋችንን ማጣት የለብንም፡፡

የሴቶች አገልግሎት፡- የጳውሎስን መልእክት በማመላለስ፣ ትንሳኤውን በማብሰር 36ቱ ቅዱሳን አንስት በወንጌል አገልግሎት ላይ በመተባበር . . .

የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ዘዳ 4፡9-10 መርሃ ግብር መምራት ማስተባበር መዘመር ቅዳሴና ጸሎቶች ማህሌቱ ላይ በመሳተፍ

የአገልግሎት ሕይወት ሉቃ 12፡42 1ጢሞ 3፡5

·         በአገልግሎት መሰልቸት ምንድን ነው? መንፈሳዊ ዝለትስ? የሚሰለቹ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?

በሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኘው የወጣቱ ሕብረት ትልቅ ኃይል ስለሆነ ለቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤትን ትልቅ ስራን መስራት የሚችል ጥሩ አደረጃጀት ያለው ብርቱ ተቋም አድርጎታል፡፡

ከኦሪት ጊዜ ጀምሮ ልጆችና ወጣቶች በጉብዝና ወራት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማሩና በጋራ እንዲሰባሰቡ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳስባል ዘዳ 4፡9-10

የክህነት አገልግሎት

-       በአሁኑ ጊዜ ክህነት ለሁሉ ሕዝብ ዘርን ሳይመርጥ ተባእት ጾታ ለሆነ ሁሉ የሚሰጥ ሲሆን፤ በፊት ዘር ከፈቀደ ብቻ ካህን መሆን ሲቻል አሁን ግን እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲሆን ብቻ በክህነት እርሱን ማገልገል እንችላለን፡፡

-       ለመምከር፣ ለመገሰጽ፣ ለመስበክ፣ ለማጽናናት፣ ለማጥመቅ፣ ስጋ ወደሙን ለማቀበል፣ ቤተክርስቲያንን በማስተዳደር የጸሎት ስርዓቶችን ለመምራት፣ በቅዳሴ በማኅሌቱ ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ሆነው የሚያገለግሉ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ተሳትፎ ያላቸው ታላቅ አገልጋዮች ናቸው ካህናት (ከድቁና እስከ ጵጵስና)፡፡

-       አንድ ካህን በአገልግሎቱ ሉቃ 12፡42፣ 1ጢሞ 3፡2-8፣ ሮሜ 15፡16፣ ቲቶ 1፡7 እኚህንና የመሳሰሉትን ነጥቦች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡ ከምንም ነገር በላይ ለመንጋው የሚራራ መሆን ይኖርበታል፡፡

-       የምናገለግለው ለምንድን ነው? ዘለዓለማዊ መንግሥት ምንድን ነው?

-       በአገልግሎት መሰላቸትና መንፈሳዊ ዝለት ከምን ይመጣል? አገልግሎት የሚሰለቻቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው የማይሰለቻቸውስ?

o   ጥያቄዎች

-       አገልግሎት ምንድን ነው?

-       አገልግት እንዴት እናገለግላለን?

-       ምን ዓይነት አገልግሎት

-       አገልግሎት ለምን እናገለግላለን? ባናገለግልስ ምን እንጎዳለን? የማገልገል ጥቅሙስ ምንድን ነው?

-       በአገልግሎት መሰላቸት ምክንያቱ ምንድን ነው? ለምን እንሰለቻለን? እንዳንሰለች ምን ማድረግ አለብን? ምን ዓይነት አገልግሎት ነው የማይሰለቸን? የሚሰለቹና የማይሰለቹ ሰዎች ልዩነታቸው ምኑ ላይ ነው?

-       የምናገለግለው በምን ሰዓት ነው? በሙሉ ሰዓት ማገልገል ምን ማለት ነው?

-       የቅዱሳን አባቶቻችን አገልግሎት ከእኛ አገልግሎት የሚለዩባቸው ነጥቦች ምን ምን ናቸው? እኛስ እንደ እነርሱ ለማገልገል ምን ማድረግ አለብን?

-       አገልግሎት የምንሰጥበት ቦታ የት ነው? ለምን ዓይነት ሰዎች ነው?

-       በአገልግሎት የምናገኘው ዓብይ ጥቅም ምንድን ነው? ጉዳትስ አለው ወይ?

-       አገልግሎት ውስጥ ለመግባት ምን ያስፈልጋል? ከአገልግሎት በፊት፣ ውስጥና ድሕረ አገልግሎት አገልጋይ ምን መምሰል አለበት?

-       ወደ አገልግሎት እንዳንሄድ የሚገዳደሩን ነገሮች ምን ምን ናቸው?

-       የአገልግሎት ምርጫ፣ ጸጋና የክፍል ምደባ ምንድን ነው? እንዴት እንወስናለን እንመርጣለን?

-       ለወደፊት ምን ማድረግ አለብን?

-       አገልጋይ ለቤተሰብና ለሕብረተሰቡ ትልቅ አርአያ ነው፡፡

 

“እኔ ለእነርሱ መምህር ነኝ በአንተ ክፍል ውስጥ ግን ተማሪ ነኝ፤ እኔ የእነርሱ እረኛ ብሆንም ከአንተ መንጋ በጎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡” ቅዱስ አውግስጢኖስ

Monday, May 20, 2013

ግዕዝ (Ethiopic)

The Ethiopic Alphabet
By Dr. Aberra Molla (ዶ/ር ኣበራ ሞላ)
Ethiopia has its own ancient alphabet. According to the beliefs of the Ethiopian Orthodox Church, Ethiopic or Geez is one of the ancient alphabets and languages. The first human to use the alphabet is believed to be Henoch of the Old Testament. Henoch supposedly wrote the Book of Henoch in Ethiopic around c. 3350 BC. In the Ethiopian Orthodox view, the Book of Enoch (መጽሓፈ ሄኖክ) was written in Ethiopic by Enoch, considered the oldest book in any human language. The original forms of the letters themselves were said to have been invented by the even earlier ancestral figure, Henos.
History
Ethiopic is an ebugida meaning that each symbol represents a consonant and vowel combination. The symbols are organized into classes and orders of similar symbols, which are associated with similar sounds. The symbols are organized on the basis of both the consonant and the vowel. Ethiopic is written left to right across the page. These Ethiopic characters have evolved over time from more ancient forms.
There is archeological evidence that the proto-Geez alphabet existed before the 9th century BC especially during the D`mt (ደኣማት) Kingdom in Northern Ethiopia. The ancient character set existed as the Heleheme series having only a first order. The first and last syllographs of Geez, He () to Pe () are relatively the same in Ancient Egypt as the first and last main Hieroglyphs. The order of the Geez system has remained the same for roughly 3000 years. Some believe that the first character set was an ebugida.
Others even claim that the classic Ethiopic with its seven vowel expansions was in existence before 3000 BC. Still others claim that Ethiopic is a Sabean alphabet. It is thought by some that it was during the Axumite Kingdom of around 340 AD that the alphabet gained the vowel forms and started to be written from left to right.
Each character has its own numeric value.
The Axum Stone
Languages
Translation of Bible books into Ethiopic, the ancient Semitic language, contributed to the development of the syllabic alphabet. Gradually, the Geez language started to lose its prominence and now remains primarily as a liturgical language of the Ethiopian Orthodox Church. Around the 13th century AD, Amharic became the dominant language. As a result, more characters were added to Geez primarily through the influence of the Hamitic languages. In the 1800's the Bible was translated to Amharic and later to Tigrigna and Oromo languages. Since then Ethiopic has added more characters as more languages began using it.
Ethiopic, an abjad abugida syllabary, has been in use by numerous languages of Ethiopia such as Agew, Amharic, Bilen, Geez, Harari, Me'en, Sebat Bet Gurage, Silte, Tigre and Tigrigna. The Bible, complete or in part, has also been published in Ethiopic in most of the above languages and others such as Gedeo, Hadiya, Kembata, Oromo, Sidamo and Welayta languages since 1513. Character Sets
The Ethiopic character set has numerous subsets with their own character sets. It includes the Geez language set.
 
 

The most commonly used Geez is the Amharic alphabet. The picture above is Amharic characters and numerals without the "V" series. Apart from this "Classic" set that was popularized by Tesfa Gebresellassie Printing Press since 1917 E.C., there is now an "Abridged" (Haddis / ሃዲስ) Amharic set.
Syllables
Syllables have their own names.
Symbols
Numerals
The digits have their own names. An example is available at: http://www.ethiopic.com/ETHIOPIC/numerals.htm
Notation
Pronunciation
Ethiopic is a syllabic alphabet and each character represents a separate sound. However, there are a few characters that represent the same series of sound.
The characters are related in three dimensions.
I. The first order characters have simple or the basic character shapes.

II. The other order characters have dashes, circles, etc. additions in almost a uniform pattern for orders.
III. The pattern of the sound of the characters is the same within an order. 
ሀ     HE - as in hurt
ሁ     HU - as in hood
ሂ     HI - as in hit
ሃ     HA - as in hat
ሄ     HIE - as in hen
ህ     H - the "h" sound as in dahlia
ሆ     HO - as in hot
ሇ    HWO - as in whole

Some Ethiopic users have drifted from these basic dimensions and problems have crept in to the usage of two groups of first order characters. Characters involved in this error are "ሀ", "ሐ", "ኀ", "አ" and "ዐ" as these glyphs erroneously share the sound with their respective fourth order form varieties. Ethiopic characters do not share sound across orders and thus "ሀ" and "ሃ" as well as "አ" and "ኣ" do not share the same sound. First order phenomes are expressed by opening the mouth only slightly while fourth order phemones are relatively more explosive requiring more opening of the mouth. The true sound of the Geez "አ" is "EA" as in "earth". "ኧ" is "EWA" It is most likely confusion with the wrong usage of "ሀ" as "HA" (instead of "HE" or "ኸ") that forced Unicode to refer to "ሃ" as "HAA" to differentiate it from "ሃ" or "HA". It is because "ሀ" and "ኸ" share the same "HE" sound that "ሃ" and "ኻ" share the "HA" sound or "ሆ" and "ኾ" share the "HO" sound.
Another example is the wrong spelling of "Abeba" as "Ababa" probably on the assumption that "በ" should be spelt as "ba" if the spelling of "ሀ" is "ha". The right spelling of "Addis Abeba" is "ኣዲስ ኣበባ" in Amharic and "Addis Abeba" in English. This is also the way I knew it in my geography lessons. This misspelling has also metastasized and an instance is "Asmera" spelt as "Asmara". In the near future Ethiopic will take advantage of speech and character recognition. This is thus the time to tackle the misunderstanding and rectify the Amharic and English errors, at least for the new smaller sets and digitized documents.

The Ethiopic Glyphs:
The glyphs are very close to the Latin alphabet in shape and size. The set consists of syllables, numerals, symbols and notation marks. There are typefaces, but no capitalization.
 

 
0
1
2
3
4
5
6
7
8
9
A
B
C
D
E
F
120
121
122
123
124
 
 
 
125
 
 
 
 
126
127
128
 
 
 
129
12A
12B
 
 
 
 
12C
 
 
 
 
12D
 
12E
12F
130
131
 
 
 
132
133
134
135
 
 
 
 
136
137
 
 
 
138
139
 
 
 
 
 
 
2D8
2D9
 
 
 
 
 
 
 
 
 
2DA
 
 
2DB
 
 
2DC
 
 
2DD
 
 
  The Ethiopic Character Set, 2002 ግዕዝ ethiopic.com ኣበራ ሞላ 8/30/08



















The Sorting Order
A good working example of Ethiopic sorting by Elfalem is available at http://elfalem.tripod.com/.
Ethiopian Multiplication

 
The Ethiopic Printing Press
The introduction of the printing press around 1900 encouraged the proliferation of books. Books and newspapers were printed using type-setting technology. Type-setting provided a fairly faithful reproduction of the Ethiopic characters, which prior to the introduction of the printing press, were written by hand. Type-setting is similar to utilizing the "a", "b", "c"...characters except for the use of the "ሀ", "ሁ', "ሂ"... characters.
Ethiopic Computerization
With the advent of computer technology, it became possible to efficiently produce printed documents having Ethiopic characters without the use of the a printing press. Dr, Aberra Molla developed a method of rendering a greater variety of Ethiopic characters in the 80's. A single Ethiopic or Geez set was distributed on character sets equivalent to more than eight English character sets. Dr. Molla's method included using the function keys to alter the font in which a default character is rendered. The different fonts indicated, by convention, that different character orders were specified. Two new layouts were presented to go along with his novel use of the computer. One was close to the Amharic typewriter layout while the characters were Ethiopic. The other was somewhat similar to the Ethiopic character sound of the English keyboard characters. The first Ethiopic publisher for DOS with which Ethiopic was computerized was released in 1987 as ModEth. In 1993 the concept was moved to EthioWord, an add-on to Microsoft Word for Windows.
 



 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 


The Amharic character set has some redundant series with similar sound. These redundant characters were assigned to the symbol keys until they were recently moved to the vowel keys. Each of the more than 564 glyphs are typed with no more than two keystrokes. The set includes Latin characters and novel glyphs.
The Amharic Typewriter
In 1714, Henry Mill obtained a patent, number 395, in Britain for a machine he invented that appears to have been similar to a typewriter. http://www.todayinsci.com/M/Mill_Henry/MillHenryPatents.htm
The machine continued to be improved and became invaluable and Emperor Menelik received one. Ethiopians soon realized the need to have a similar machine for the Amharic alphabet and numerous studies and meetings followed for decades. Since the large number of the Amharic characters made it impossible to fit the characters on the keys of the English typewriter, attempts revolved around cutting down the glyph numbers. One proposal involved keeping the first order characters only and replacing the other orders with a few characters to be used like vowels just like the Latin system. Another one was to modify the shapes of the characters into a uniform pattern so that the vowel forms look alike and can be changed to their orders by ligating small parts to the first order improved glyphs.  Ethiopian scholars, officials and authors that worked on these projects close to a century include Emperor Menelik, Ato Alemu Haile Mariam, Ato Areaya Birru, Dr. Aleme Worq, Aleka Kidane Wold Kifle, Blata Mersie Hazen Wolde Kirkos, Leaul Ras  Imru, Ato Million Neqniq, Ato Haddis Alemayehu, Ato Abebe Reta, Ato Zewdie Gebre Mariam, Ato Seifu Feleke, Ato Samuel Terefe, Blata Wolde Giorgis, Engineer Ayana Birru, Dr. Abreham Demoz, Ato Tekle Mariam Fantaye, Dr. Amsalu Akllilu, Ato Leaul Seged Alemayehu, Meto Aleqa Yigezu Bisrat, Ato Fantu Bekele and Ato Amanuel Abreham. 
The issue remained unresolved while Ayana Birru came up with an incomplete Amharic set by creating a method whereby characters were created by ligating small parts to glyphs on printing by addition of smaller parts. These incomplete and weird characters did rescue the Amharic characters, even though they were not Amharic, by maintaining uniformity. Recently these fake parts have even been computerized to incomplete Amharic typewriter sets by dozens of individuals who were replacing an ASCII set with some characters and character parts. In spite of all these, attempts to modify the English typewriter print head for Amharic by ligation methods failed while reducing the character numbers or modifying the glyph shapes was equally hopeless and never materialized. Fortunately, these Amharic typewriter glyphs and their difficult typing methods have become obsolete because Ethiopic was computerized by Dr. Aberra Molla and that revolutionized the Geez script. As a result, the long and hard unsuccessful struggles by Ethiopians to use the English typewriter that ultimately became the computer keyboard for use with Amharic became a reality in the 80's and surpassed the imagination of the previous generations of Ethiopians by accommodating more characters and many languages that use the Geez alphabet.