የኖህ ድንቅ መርከብ
በነብይ ተነግሮ ነበር በብሉይ
አምላክ እንዲመጣ ከላይ ከሰምይ
ሃጢያት ያለነካትን ዘርን አስቀርቶ
... ለራሱ መረጣት ማደሪያው አድርጎ
ከስጋዋ ስጋ ከደሟ ደም ነስቶ
ወደ ምድር መጣ ፍጹም ሰውም ሆኖ
ምስጋና ይድረሳት ለእመቤቴ ማርያም
ምክንያት ለሆነች ድህነት ለዚህ አለም
ፍጥረትም በሙሉ ክብርን የሰጧታል
ወላዲተ አምላክ ኪዳን ነሽ ይሏታል
አንቺ ነሽ እማማ ልምለሚቷ በትር
የያቆብ መሰላል የኖህ ድንቅ መርከብ
ልበ ቅን እኮ ነሽ ለሁሉ ይምታዝኒ
በልጅሽ ፊት ቆመሽ የምትማልጂ
ጎዶሏችን ሞልቷል በአንቺ እዚያ መገኘት
ከልጅሽ ጋር ሆነሽ በዶኪማስም ቤት
ጽዮን እመቤቴ የሁሉ መጠጊያ
ከሴቶች ተመርጠሽ ሆነሻል ማደሪያ
አምላክም ወድደው ፍጹም ማንነትሽን
እርሱን የምትፈሪ ልበ ቅንንትሽን
እርሱን የምትፈሪ ልበ ቅንነትሽን
~~~~~+++++~~~~~~
ምንጭ:- ኢትዮሃበሻንስ ፌስቡክ ዎል
No comments:
Post a Comment